You are here መግቢያ
ሙስሊሞች ለዓለም ስልጣኔ ምን አበረከቱ? (ክፍል 8)

ሙስሊሞች ለዓለም ስልጣኔ ምን አበረከቱ? (ክፍል 8)

7. ግብርና

ሙስሊም ሳይንቲስቶች በርካታ የተክል ዓይነቶችን ገልፀዋል። በ 12ኛው ...

ሙስሊሞች ለዓለም ስልጣኔ ምን አበረከቱ? (ክፍል 7)

ሙስሊሞች ለዓለም ስልጣኔ ምን አበረከቱ? (ክፍል 7)

5. ሕክምና

ሙስሊሙ በጤና ላይ ያለው ፍላጎት በቀጥታ ከኢስላም አስተምህሮ የመነጨና...

ሙስሊሞች ለዓለም ስልጣኔ ምን አበረከቱ? (ክፍል 6)

ሙስሊሞች ለዓለም ስልጣኔ ምን አበረከቱ? (ክፍል 6)

6.ሙስሊሞች ካበረከቱት አስተዋጽኦዎች ንዑስ ምሳሌዎች

አሁን ደግሞ ሙስሊሞች በዋና...

ሙስሊሞች ለዓለም ስልጣኔ ምን አበረከቱ? (ክፍል 5)

ሙስሊሞች ለዓለም ስልጣኔ ምን አበረከቱ? (ክፍል 5)

ታሪካዊ መገለጫዎች

በመጀመሪያ ገፆች እንደተመለከትነው ቁርዐንና የነብዩ አስተምህሮ...

የልጆች አስተዳደግ በኢስላም (ክፍል-4)

የልጆች አስተዳደግ በኢስላም (ክፍል-4)

አዲስ ከተወለደ ልጅ ጋር የሚያያዙ ነገሮች

አንድ ወላጅ ልጅ ሲወለድለት ምን ማድረ...

የነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) የአመራር ብቃት

የነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) የአመራር ብቃት

ነቢያዊ አመራር ስንል ዘመናዊ የአመራር ንድፈ ሀሳብና ስልትን ከነቢዩ ሙሀመድ (...

የቁርኣን ታሪክ

የቁርኣን ታሪክ

ቁርአን ንፁህ የሆነ የአላህ ቃል (ንግግር) ነው። በቁርአን ውስጥ የአላህ ቃል ያልሆነ ነገር የለበትም። ቁርአን የኦርጅናል ባህርይውን እንደያዘም ዛሬን ሊደርስ ችሏል። ወደ ሰነድነት ሲቀየርም በረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የበላይ ተቆጣጣሪ አማካኝነትነት ነው። እያንዳንዱ ምዕራፍ የት መቀመጥ እንዳለበት ለፀሀፊዎቻቸው ትዕዛዝ ይሰጡ ነበር። በዚህም ሁሉም የቁርአን ምዕራፎች በረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ትዕዛዝ ተደርድረው የተቀመጡ ናቸው።

አንድ ሙስሊም ሊያደርጋቸው የሚችል ከ200 በላይ በጎ ሥራዎች

አንድ ሙስሊም ሊያደርጋቸው የሚችል ከ200 በላይ በጎ ሥራዎች

1.በየቀኑ ከቁርዓን የተወሰነ ክፍል ማንበብ

2.በመስጅድ ግንባታ ላይ መሣተፍ

3.ወላጅ አልባ የሆኑ ልጆችን ማሣደግ

4.የንፁህ የዉሃ ጉድኋድ በመቆፈር ለተጠቀሚዎች ማቅረብ

5.ለአንድ በደዕዋ ሥራ ላይ ለተሠማራ ድርጅት ወርሃዊ መዋጮ ማድረግ

6.የተቸገሩ ቤተሰቦችን መርዳት

7.በደዕዋና መልካም ሥነምግባር ዙሪያ ጠቃሚ መፅሃፍ ማንበብ

በኢማን ከፍ ማለት (ክፍል 3)

በኢማን ከፍ ማለት (ክፍል 3)

የማስተንተን አስፈላጊነት

ኢማም አልገዛሊ እንዲህ ይላሉ ‹ አላህን (ሱ.ወ) ወደ ሚያሣውቀው መንገድ መጓዝ፣ ፍጥረታቱን በማስተዋል እሱን ማላቅ፣ ድንቅ ሥራዎቹን በጥልቀት ማስተንተን፣ የተለያዩ ፈጠራዎቹን በመቃኘት ግንዛቤን መውሰድ ኢማን በሰው ውስጥ እንዲረጋና እንዲሰርፅ ምክኒያት ይሆናልየተከበረውና ሀያሉ አላህ የሰው ልጆች ወደራሣቸው በመመልከት ጭምር እንዲያስተነትኑ ጋብዟል ።

ዓሹራ… የድል ውሮሸባ በበደል ላይ

ዓሹራ… የድል ውሮሸባ በበደል ላይ

ሙሓረም አስረኛው ቀን አላህ ያላቀው ቀን ነው። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አክብረውታል። ቀኑ እንዲፆም አዘዋል። “ከአላህ (ልዩ) ቀናቶች መሀል አንዱ ነው።” ብለዋል። ይህ ቀን በጃሂሊያ የተከበረ ነበር። አይሁዶች በዓል አድርገው ይዘውታል። ኢስላም ውስጥ መጀመሪያ ፆም ግዴታ ሲሆን ከረመዳን ወር በፊት እርሱ ነበር የተመረጠው።

አል-ወሰጢያ : መገለጫዎችና የትኩረት አቅጣጫዎች

አል-ወሰጢያ : መገለጫዎችና የትኩረት አቅጣጫዎች

 በመጀመሪያ አል-ወሰጢያ የሚለው ቃል የሚወክለውን ፅንሰ-ሀሳብ ከማብራረታችን በፊት ትንሽ ትርጉማዊ መንደርደሪያ ለማድረግ እንሞክር። አል-ወሰጢያ መካከለኛው መንገድ፣ ሚዛናዊ አካሄድ፣ ወርቃማ አማካይ (gloden average) የሚሉት ቃላት የሚያስተላልፉትን ትርጉም ያስተላልፋል።

የወለድ ጉድፎች (ክፍል 1)

የወለድ ጉድፎች (ክፍል 1)

የስነ-ኢኮኖሚ (የኢኮኖሚክስ) ባለሙያዎች ወለድን መሠረት ያደረገ ኢኮኖሚ አስፈላጊነቱን ለማስረዳት ብዙ ርቀት ሊጓዙና ማስረጃም ለማግኘት ይሞክሩ ይሆናል፤ ዋናው ፈተና ግን የወለድ ተጽዕኖ በግልጽ ማጥናቱ ላይ ነው። መታወቅ ያለበት ነገርም አላህ(ሱ.ወ) አንድን ነገር ሐራም ሲያደርግ (ሲከለክል) የተከለከለው ጉዳይ ምንም ዓይነት ጥቅም የለውም ማለት እንዳልሆነም ጭምር ነው።

እዝነትና ፍትህ በረሱል(ሰዐወ) ሲጣመሩ

እዝነትና ፍትህ በረሱል(ሰዐወ) ሲጣመሩ

የዚህን ታላቅ ነብይ ሁለንተናዊ ስኬት ለመረዳት ብሎም ለሰብዓዊና ቁሳዊው ስልጣኔ መነሻ የሚሆን ትውልድን በመፍጠር ሂደት ውስጥ የተከፈለውን መስዋትነት ክብደት ለመረዳት ይረዳ ዘንድ ከውልደታቸው በፊት የነበረውን ጨለማ አለም በተለይም የአረቡ ምድር ሰጥሞበት የነበረውን ባስ ያለ ጨለማ ወደ ኋላ መመልከት በራሱ በቂ ማስረጃ ሊሆን ይችላል። አለም ጥቂቶች በርካታ ሀብትን ሰብስበው ብዙዎች ግን በረሀብ አለንጋ የሚረግፉበት፣ ጥቂቶች በአምባገነንነት ስልጣንን ተቆናጥጠው ብዙዎች በባርነት ቀንበር ውስጥ ከመኖር በታች የሆኑባት አስፈሪና መራራ ቦታ ሆና ነበር።

ከኢስላም አምባሣደር ሙስዐብ ኢብኑ ዑመይር ለደዕዋ ወጣቶች የተላለፈ መልእክት

ከኢስላም አምባሣደር ሙስዐብ ኢብኑ ዑመይር ለደዕዋ ወጣቶች የተላለፈ መልእክት

ዘመን ዘመንን ቢተካ የሱ ዓይነት ስብእና ለዚህች ዓለም ማበርከት ይከብደዋል። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የሱን ዓይነት ምርጥ ሰው ለማግኘት በእጅጉ ይቸገራል። ልጅነቱንና ከፊል የወጣትነት ዘመኑን በክህደት ዓለም ፀጋዎች ውስጥ ሰጥሞ ነው የኖረው። ወደ እስልምና በገባ ጊዜ ግን ሁሉም ፀጋዎች በአንዴ ተገፈፉ። እሱም በውሣኔው ሳይፀፀት በዱኒያ ጥቅሞች ሣይታለል በእምነቱ ፀና። ከባድ ውሳኔ ነበር።

ኢማሙ ሻፊዒይ (ክፍል 2)

ኢማሙ ሻፊዒይ (ክፍል 2)

7. የዘመን ቅኝት

ከሂጅራ በኋላ ሁለተኛው ምዕተ ዓመት ሁለት ዋና የፊቅህ ትምህርት ምልከታዎች (መዝሃብ) ምስረታ ዕውን የሆነበት ጊዜ ነበር። እነሱም “አህሉር-ረዕይ”- ከቁርአንና ሐዲስ መረጃዎች በመነሳት አመክንዮን መሰረት ያደረገ አተያይና እና “አህሉል-አሰር”- ቁርአንና ሐዲስን መሰረት ያደረገ አተያይ ናቸው። የመጀመሪያው ትምህርት ቤት ንድፈ ሀሳብ ዒራቅ ውስጥ ይኖሩ በነበሩት ሰሃባ በዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ) የፊቂህ አስተምህሮት ላይ ተመስርቶ እዚያው ዒራቅ ውስጥ ያደገ የፊቅህ አይነት ነው። የኢብኑ መስዑድ ትምህርት በተማሪዎቻቸውና በጓደኞቻቸው አማካኝነት ተስፋፋ።

ሴት- እንደ እናት

ሴት- እንደ እናት

የሰው ልጅ ከሴት ጋር በሚያደርገው ግንኙነት መጀመሪያ የሚያገኘው እናቱን ነው። ዘጠኝ ወራት በሆዷ ትሸከመዋለች። አምጣ ትወልደዋለች። አድካሚ በሆነ መልኩ አጥብታ ታሳድገዋለች።

ሴትን እንደ እናት ከፍተኛ ክብር በመስጠት ኢስላምን የሚወዳደር ሃይማኖትም፣ ሥርዓትም አስተሳሰብም የለም።

ኢስላም አላህን በብቸኝነት ከማምለክ ቀጥሎ ካስተላለፋቸው ኑዛዜዎች የመጀመሪያው የእናት እንክብካቤ ጉዳይ ነው። እናትን መንከባከብን የመልካም ሥነ-ምግባሮች መሠረት አድርጐታል። መብቷ ከአባትም መብት የበለጠ መሆኑን በአጽንኦት አስተምሯል።

ኢስላምና ቤተሰብ

ኢስላምና ቤተሰብ

ኢስላም የህይወታችን ምሉዕ ገፅታ የሚዳስስ የተሟላ የህይወት መመሪያ ነው። በዚህም የተነሳ ቤተሰብን እንደ አንድ የማሕበረሰቡ የማእዘን ድንጋይ አድርጎ ይመለከታል። ፍቅር፣ መስዋእትነት፣ ታማኝነትና መተሳሰብ መገለጫዎች ናቸው።

የልጆች አስተዳደግ በኢስላም (ክፍል-4)

የልጆች አስተዳደግ በኢስላም (ክፍል-4)

አዲስ ከተወለደ ልጅ ጋር የሚያያዙ ነገሮች

አንድ ወላጅ ልጅ ሲወለድለት ምን ማድረግ ይኖርበታል?

ከአላህ (ሱ.ወ) የተሰጠን ምርጡ ሸሪዓችን ከመሰረታዊ ዕውቀት ከትንሽ እስከ ትልቅ ምንም ያስቀረብን ነገር የለም።

ልጅን በተመለከተም አሳዳጊዎችና ወላጆች በእውቀት ላይ ተመስርተው እንዲንቀሳቀሱ ከተወለደበት ጊዜ አንስቶ

አቡ ዐብዱላህ አል-በጣኒ

አቡ ዐብዱላህ አል-በጣኒ

አቡ ዐብዱላህ ሙሀመድ ኢብኑ ጃቢር ኢብኑ ሲናን አል-በጣኒ አል-ሀራኒ እ.እ.አ. በ 858 በሀራን ነው የተወለደው። የሀራን ግዛት ከሆነችው በጣን የተገኘ አንድ ዘገባ እንደሚለው ከሆነ በጣኒ መጀመሪያ ትምህርቱን የተከታተለው በያኔው ዘመን እውቅ ሣይንቲስት ከነበረው ከአባቱ ጃቢር ኢብኑ ሰንዓን አል-በጣኒ ነው። ቀጥሎም ወደ ረቃ በመሄድ በኤፍራተስ ወንዝ ዳርቻ ኑሮውን አደረገ። እዚያም በነበረው ቆይታ ከፍተኛ የሆነ እውቀት በመቅሠም ታላቅ ምሁር እስከመሆን ደረሠ። በ9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ወደ ሣመራ በመሄድም እስከ ህይወቱ ፍፃሜ ማለትም እስከ 929 ድረስ እዚያው ቆየ። አል-በጣኒ የዘር ግንዱ ከሳባውያን ሲሆን እርሱ ግን ሙስሊም ነበር።

ታላቁ የበድር ጦርነት (ክፍል 1)

ታላቁ የበድር ጦርነት (ክፍል 1)

ታላቁ የበድር ጦርነት በአምስተኛው አመተ ሂጅራ በተቀደሰው ወርሃ ረመዳን 17 ላይ የተካሄደ እውነት ከሐሰት የተለየበት ታላቅ ክስተት ነው። ታሪኩን እነሆ…

የመካ ቁረይሾችንና በተግባር መሠሎቻቸው የሆኑትን ያካተተው የጣኦት አምላኪው ማህበረሰብ ሙስሊሞችን እና ጉዳያቸውን ሁሉ ከመካና ዙሪያዋ ከሚገኙ አካባቢዎች ካባረሩ በኋላ በየስሪብ (መዲና)ም ቢሆን እምነታቸውን በነፃነት ያስፋፉና ይተገብሩ ዘንድ እንደማይተውዋቸው የአላህ መልእክተኛ እና ሙስሊሞች ጠንቅቀው ያውቁ ነበር። በመሆኑም ለክፉ ነገር ሁሉ እራሣቸውን ማዘጋጀት እና መጠንቀቅ ጀመሩ።

ሙስሊሞች ለዓለም ስልጣኔ ምን አበረከቱ? (ክፍል 8)

ሙስሊሞች ለዓለም ስልጣኔ ምን አበረከቱ? (ክፍል 8)

7.ግብርና

ሙስሊም ሳይንቲስቶች በርካታ የተክል ዓይነቶችን ገልፀዋል። በ 12ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ የኖረው አል-አዋም 585 የተክል ዓይነቶችን የጠቀሰ ሲሆን የተለያዩ ፍራፍሬዎች እንዴት እንደ ሚዘሩም ትንተና ሰጥቷል። አንዳንድ ምሁራን ጥናታቸውን ያካሄዱት ወደሐጅ በሚያደርጉት ረዥም ጉዞ ነበር። በዚህ በኩል አቡል ሀሰን አልነባቲ ተጠቃሽ ነው።

በተግባራዊ ዘርፍ፣ የመስኖ ሥራን አሳድገዋል። የተፈጥሮ ማዳበሪያ ተጠቅመዋል፣ እንዲሁም የከብት እርባታን አሻሽለዋል። ለምእራቡ ዓለም ኮክን፣ ጥጥን፣ ሩዝን፣ ሙዝን፣ እና የሸንኮራ አገዳን ያስተዋወቁት ሙስሊሞች ናቸው።

በኢሰላማዊት እሰፔን አሳን ለምግብነት የሚያረቡ ሠው ሰራሽ ሀይቆች የተለመዱ ነበሩ።[1]

PAUSE- ፓውዝ -PLAY

ሲስቁ ሲያውካኩ፣ ሰዎች በአንድ ጉዳይ

ጥርሳቸውን ከፍተው፣ ድዳቸው እስኪታይ

አፋቸውን ከፍተው በሆታ ሲያፏጩ

ከአይኖቻቸው ፈሳሽ እንባ እየተራጩ